መዝሙረ ዳዊት ም፥፳፪
፩ እግዚአብሄር እረኛየ ነው የሚያሳጣኝ የለም።
፪ በለመለመ መስክ ያሰማራኛል፤ወደእረፍት የመስኖ ዉሃም ይመራኛል።
፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለስሙም በፅድቅ መንገድ መራኝ።
፬ በሞት ጥላ መካከል እንኴ ብሄድ፣አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉዉን
አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያፅናኑኛልና።
፭ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፣በጠላቶቼ ፊት ለፊትም ራሴን በዘይት ቀባህ።
፮ ቸርነትህና ምህረትህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ ይከተሉኛል፥
በእግዚአብሄር ቤትም ለዘለአለምእኖራለሁ።
|
| 112. ምዕራፍ 112 አል-ኢኽላስ፡፡ ክፍል 30፡፡
112ኛ ሱረቱ አል-ኢኽላስ፤ (የፍጹምነተ ምዕራፍ)፡፡
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ (አንቀጾችዋ) 4 ናቸው፡፡
1. በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡
2. «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡
3. «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡
4. «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»
103. ምዕራፍ 103 አል-ዐስር፡፡ ክፍል 30፡፡
103ኛ ሱረቱ አል-ዐስር፤ (የጊዜያት ምዕራፍ)፡፡
በመካ የወረደች ናት፤ አያትዋ (አንቀጾችዋ) 3 ናቸው፡፡
1. በጊዜያቱ እምላለሁ፡፡
2. ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡
3. እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ
የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡
|
|